For best view click on full screen below
ke ayen yawetachu zehabeshawoch……bertu…. konjo gazeta new/…
አሮጌው ዓመት ተሰናብቶ አዲስ ዓመት አሀዱ ባለ ማግስት ነው፤ መስከረም 1ለመስከረም 2 አጥቢያ፤ ሰዓቱ ደግሞ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሆኗል፡፡ ከቢጣ ገነት ወረዳ አላሞ በመባል ከሚታወቀው በረሃማ አካባቢ አንድ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ቢጣ ገነት በከፋ ስር የምትገኝ ወረዳ ስትሆን፤ በዓለም ላይ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘባትም እንደሆነ በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ወቅቱ የፀደይ ወራት መግቢያ ቢሆንም ሰማዩ ግን ኩልል ብሎ አልጠራም፡፡ ደመናው እንዳዘለ ነው፡፡ ይዘንባል፡፡ በጉምና በካፊያ በተደናገዘው በእዚያ ውድቅት ሌሊት የ60 ዓመት አረጋዊና የ28 ዓመት ወጣት የሆኑት አባትና ልጅ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው በእንቅልፍ ላይ ሳሉ በዱላና በጠመንጃ ተመተው በጣር መሀከል ተገኙ፡፡ በወቅቱ አንድ የ6 ዓመት ልጅ በመሀከላቸው ተኝቶ የነበረ ቢሆንም በእርሱ ላይ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰበትም፡፡ የወንጀሉ መከሰት መረጃ የደረሰው የቢጣ ወረዳ ፖሊስ በአፋጣኝ ወደ ስፍራው በመንቀሳቀስ በጣር ላይ የሚገኙት አባትና ልጅ ከወደቁበት ስፍራ ደረሰ፡፡ የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት ለማወቅም ደፋ ቀና በማለት ጆሮውን ደቀነ፡፡ ሆኖም እንዳሰበው ሊሳካለት አልቻለም፡፡ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰባቸው መናገር ሳይችሉ የ28 ዓመቱ ወጣት ከሰዓታት በኋላ ሕይወቱ አለፈ፡፡ የ60 ዓመት አዛውንት አባቱም በከፍተኛ ስቃይ ለሁለት ቀናት ሲያጣጥሩ ቆይተው እሳቸውም ሞቱ፡፡ ………. Page 26 lay yaew yewenje tarik hulum liyanebew yemigeba new…..
ke ayen yawetachu zehabeshawoch……bertu…. konjo gazeta new/…
አሮጌው ዓመት ተሰናብቶ አዲስ ዓመት አሀዱ ባለ ማግስት ነው፤ መስከረም 1ለመስከረም 2 አጥቢያ፤ ሰዓቱ ደግሞ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሆኗል፡፡ ከቢጣ ገነት ወረዳ አላሞ በመባል ከሚታወቀው በረሃማ አካባቢ አንድ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ቢጣ ገነት በከፋ ስር የምትገኝ ወረዳ ስትሆን፤ በዓለም ላይ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘባትም እንደሆነ በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
ወቅቱ የፀደይ ወራት መግቢያ ቢሆንም ሰማዩ ግን ኩልል ብሎ አልጠራም፡፡ ደመናው እንዳዘለ ነው፡፡ ይዘንባል፡፡ በጉምና በካፊያ በተደናገዘው በእዚያ ውድቅት ሌሊት የ60 ዓመት አረጋዊና የ28 ዓመት ወጣት የሆኑት አባትና ልጅ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው በእንቅልፍ ላይ ሳሉ በዱላና በጠመንጃ ተመተው በጣር መሀከል ተገኙ፡፡ በወቅቱ አንድ የ6 ዓመት ልጅ በመሀከላቸው ተኝቶ የነበረ ቢሆንም በእርሱ ላይ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰበትም፡፡
የወንጀሉ መከሰት መረጃ የደረሰው የቢጣ ወረዳ ፖሊስ በአፋጣኝ ወደ ስፍራው በመንቀሳቀስ በጣር ላይ የሚገኙት አባትና ልጅ ከወደቁበት ስፍራ ደረሰ፡፡ የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት ለማወቅም ደፋ ቀና በማለት ጆሮውን ደቀነ፡፡ ሆኖም እንዳሰበው ሊሳካለት አልቻለም፡፡ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰባቸው መናገር ሳይችሉ የ28 ዓመቱ ወጣት ከሰዓታት በኋላ ሕይወቱ አለፈ፡፡ የ60 ዓመት አዛውንት አባቱም በከፍተኛ ስቃይ ለሁለት ቀናት ሲያጣጥሩ ቆይተው እሳቸውም ሞቱ፡፡ ………. Page 26 lay yaew yewenje tarik hulum liyanebew yemigeba new…..