Amharic
የመለስ ዜናዊ ድንቀኛ ተረቶች
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በተካሄደው በ‹‹ ዓለም አቀፉ የኤኮኖሚ ስብሰባ ላይ›› የግፍ ገዢው የፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ አርቲ ቡርቲ መነባንብ:
…በኔ እምነት በታሪክም ሆነ በቲዎሪ የኤኮኖሚ እድገትና ዴሞክራሲ ቀጥተኛ ግንኙነትም ሆነ ተዛምዶ የላቸውም፡፡በኔ አመለካከት፤ በኤኮኖሚ እድገት ላይ የሚያስከትለውን ጫና ገሸሽ አድርገን ዴሞክራሲ በራሱ ጥሩ ነገር ነው፡፡በኔ አመለካከት አፍሪካውያን በጣም ስብጥሮች ነን፡፡ ስለዚህም ነው ብዬ አምናለሁ በመሃላችን ያለውን ግንኙነት ሰላማዊ የሚያደርገው፡፡እነዚህን ስብጥር ሰዎች በአንድነት ለማቆየት ያለው አማራጭም ዴሞክራሲ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ስለዚህም ዴሞክራሲን መዘርጋት ይኖርብናል: ያ ግን ለእደገት ብለን አይደለም፡፡ዴሞክራሲን መዘርጋት ያለብን ስብጥር የሆኑትን በአንድነት ለማቆየት እንድንችል ነው፡፡ የኔ አመለካከት ይሄ ነው፡፡ያም ሆኖ ግን በዚህ የምሽት ተረት ተረት፤የእንቅልፍ ማምጫ ተረብ እና የኤኮኖሚን ልማትና ዴሞክራሲን የሚያገናኝ ፈጠራና የውሸት ተረት አላምንም፡፡በታሪክ ይህንየሚያረጋግጥ መሰረት የለም: በኔም አመለካከት ከልማት እድገት ጋር የሚያገናኘው መሰረት የለም፡፡ ይህንን የቅዠትክርክር ማካሄድ ጨርሶ አያስፈልግም: ምክንያቱም ዴሞክራሲ ብቻውን ቆሞ ብቻውን ሊያበራ ይችላልና፡፡
ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የኤኮኖሚ ዕድገትን ከዴሞክራሲ ጋር የተገናኘ ነው ብለው ““የቅዠት ተረት ተረት” የተናገሩት ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2009 በጋና አክራ ይሄ ነው፡፡
ልማት በመልካም አስተዳደር ላይ ይመሰረታል፡፡ታሪክ ትክክለኛውን ውሳኔ ያመላክተናል፡፡የሕዝቦቻቸውን ፍላጎትየሚያከብሩ፤በሕዝቦች ፈቃደኝነት የሚያስተዳድሩ በሃይልና በማንአለብኝነት ከሚገዙ የበለጠ ልማታዊ ፤ የበለጠየረጉ፤እና የበለጠ ስኬታማ ናቸው፡፡ መሪዎች ራሳቸውን ለማሳበጥና በሃብትም ለመክበር ጥረት የሚያደርጉ ከሆኑ፤ ማንኛውም ሃገር ሃብት ሊኖረው አይችልም፡፡ፍትህ የሕግ የበላይነት በሚጨፈለቅበትና በሙስናና በሌብነት በተመሳቀለ ሃገር ውስጥ ለመኖር የሚመኝ ማንም የለም፡፡ ይህ አይነቱ ሁኔታ ያለበት የዴሞክራሲ ሃገር ሳይሆን የግፍ ሃገር ነው፡፡ያንን የመሰለውን አስከፊ ስርአት መገላገያው ደግሞ አሁን ነው… በ21ኛው ክፍለ ዘመን፤ችሎታ ያላቸው፤ታማኝነትያላቸው፤እና ግልጽነትን የሚቀበሉ ኢኒስቲቲዩሽኖች ለዚህ ስኬት ቁልፍ ናቸው፡፡—–ጠንካራ ፓርላማ፤ታማኝ የሆነየፖሊስ ሃይል፤ነጻና ለራሳቸው ሕሊና የሚገዙ የፍትህ ስርአት አባላት፤ነጻና ዴሞክራሲያዊ ፕሬስ፤ ንቁና ልማታዊ የሆነየግል ዘርፍ፤የሲቪል ማህበረሰብ፡፡ ለዴሞክራሲ ነፍስ የሚዘሩበትና መከታ የሚሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕብረተስቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አስፈላጊው ይሄው በመሆኑ፡፡…. ታሪክም ከነዚህ የአፍሪካ ጀግኖች ጋር ይቆማል እንጂ ራሳቸውን በሥላጣን ለማክረም ግፍ ከሚሰሩትና ለግለሰብ ፍላጎታቸው አመጽ ከሚያስነሱትና ሕገ መንግስቱን እንዳሻቸው ከሚያመሳቅሉት ጋር አይሰለፍም፡፡አፍሪካ ጡንቸኞች አየስፈልጋትም፤የሚያስፈልጋት የፈረጠሙ ዴሞክራሲያዊ ኢንስቲቲዩሽኖች ነው፡፡አፍሪካ የተሻለና ስፋት ያለው እድገት እንደሚኖራት ጥርጥር የለኝም፡፡
እኔ የምወዳችው ተረቶች
እንደሌላው ሰው እኔም የእንቅልፍ ማምጫ ተረቶች እወዳለሁ፡፡ የምመርጠው ደግሞ “ፒኖኪዮ በአፍሪካ” የተሰኘው፤ ነው:: ከአሻንጉሊትነት ወደ ሰውነት መለወጥ የሚመኘውን ፒኖኪዮ ሰው መሆን ሊችል ይችላል ግን ተአማኒነት ይጠበቅበታል፡፡ ፒኖኪዮ መዋሸት በጣም ይወዳል ያውም ገደብ የሌለው ትላልቅ ውሸት፡፡ፒኖኪዮ በዋሸ ቁጥር አፍንጫው ይረዝማል፡፡
‹‹ፐፍ: ዘ: ማጂክ ድራጎን እና ሕያው የሆኑ ውሸቶች ሃገር›› የተባለዉን ተረት እወደዋለሁ፡፡ ፐፍ: በቤቷ ያለውን ችግር ለመሸሽ የምትፈልገውን ሳንዲ የተባለች ልጅ ሕያው የሆኑ ውሸቶች ሃገር ወሰዳት፡፡ በዚያም ፒኖኪዮንና ጂብ መጣ እያለ በዉሸት የሚያስፈራራውና የሚጮኸውን ልጅ አገኘች:: ከዚያም ሌላ ማንም አይቶ የማያውቀውን ወይን ጠጅማ ላምና: ሮዝማውን ዝሆን አየች፡፡
ጥንታዊውን የኢትዮጵያ ታሪክ ተናጋሪ የኤሶፕን ግብረገባዊ ተረቶችም እወዳቸዋለሁ፡፡ ድሮ ዱሮ አንድ በጎችን ጠልፎ ለመውሰድ ችግር ያለበት ተኩላ ነበር፡፡የችግሩ መነስኤም ጠባቂው ንቁና ጠንቃቃ ስለነበር ነው፡፡አንድ ቀን ቀበሮው የተጣለ የበግ ቆዳ አገኘና ያንን ቆዳ ለብሶ በጎቹን ተመሳስሎ ከመንጋዎቹ ጋር ተደባለቀ፡፡እያደባ አንድ ባንድ በጎቹን በመብላት ላይ እያለ አንድ ቀን እረኛው አወቀበትና ከዚያን ዕለት ጀምሮ ሰርቆ ገድሎ መብላት አልቻሃለም::
ተምሳሌታዊና ድርብ ትርጉም ሰጪዎችንና የተረት አነጋገሮችን እወዳለሁ፡፡ እንደ ጆርጅ ኦርዌል የፖለቲካ ቋንቋ ያዘሉት:: ጀርጅ ሲተርት ፖለቲከኖች: ሃሰትን እንደ እውነት ግድያን የተከበረ ተግባር አድርገው ያቀርባሉ፡፡በዚህም መልኩ ጦርነት ሠላም፤ነጻነትም ባርነት፤መሃይምነት ምሁርነት፤ድህነት ሃብት፤ችጋር የተትረፈረፈ ምግብ፤ የጸሁፍ ቁጥጥርን የፕሬስ ነጻነት፤ግፍን መልካምነት፤ እያሉ ያቀርባሉ፡፡
አዎንና የልጆችን የጨዋታ ግጥምም እወዳለሁ፡-
ሃምፕቲ ዳምፕቲ የተባለ እንቁላል ግድግዳው ላይ ተቀመጠ፤ አወዳደቁም ተአምራዊ ነበር!
ጤናማ ሕብረተስብ፤ ዴሞክሬይዚ እና ንኮቹ ዲክታተሮች
“ብቸኛው ሕዝቦችን በሰላም ለማቆየት ያለው አማራጭ ዴሞክራሲ ነው” ይላል መለስ፡፡ ሃሰት ከሚኖርበት ሃገር አንዳንድ እውነተኛ ታሪኮች፡ እንመልከት-
ፍሪደም ሃውስ የዩናይትድ ስቴትስ ስቴት ዲፖርትመንት
በኤፕሪል 2008 በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ምርጫ ተካሂዶ ነበር፡ፍሪደም ሃውስ እና ፡ ያሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ባደረጉት ዘገባ መሰረት፤የተቃዋሚ ፓርቲ ተፎካካሪ ተመራጮች ከምርጫው በፊት በመንግስት ሃይላት በመንገላታትና ከምርጫው እራሳቸውን እንዲያገሉ በመያዝና መሳደድ ስቃያቸውን ይበሉ ነበር፡፡በዚህም የተነሳ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን በማግለል ስለተዉት መንግስትና ፓርቲው ብቻውን ተወዳድሮ ደጋፊዎቹ የምርጫ ተፎካካሪዎች ከፍተኝ ብልጫ አኙ፡፡ ገዢው ፓርቲ ለምርጫ ከቀረቡት ከ3 ሚሊዮን ያላነሱ መቀመጫዎች 99 በመቶውን አሸነፈ፡፡
የዓለም ባንክ (2012)
በሜይ 2010 በተካሄደው ምርጫ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ (ኢፒአርዲኤፍ) እና አጋሮቹ 99.6 በመቶ ምርጫውን በማሸነፍ የተቃዋሚውን ቁጥር በሕዝብ ተወካዮች 547 ወንበር ከ174 ወደ ሁለት አወረደው፡፡ ኢትዮጵያ በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ከሚገኙት ሃገራት በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛዋና፤ በዓለም ካሉት ድሃ ሀገራት አንዷ ነች፡፡የኑሮ ደረጃውም ቢሆን በዓለም ካሉት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ካሉትም የባሰች ዝቅተኛ ነች፡፡በዚህም በዓለም 6ተኛ ደረጃ ላይ ያለች ድሃ ሀገር ናት፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል (2009)
የኢትዮጵያ መንግስት ለሃገርም ውስጥ ሆነ ለውጭ ሃገራት እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች፤ አዲስ አሳሪና አፋኝ ሕግ አውጥቶ፤ የሰብአዊ መብትን በመግፈፍ ወንጀለኛ አድርጎል፡፡የበጎ አድራጎትና የማህበራት ሕግ (2009) የተፈጠረበት ዋነኛ መንስኤ፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፤ የሲቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ፤ለመቆጣጠርና እንቅስቃሴያቸውን ለመግታት ታስቦ ነው፡፡ይህንንም በማድረግ መጪውን የ2010ን ምርጫ ከወዲሁ ለራስ ድል ለማዘጋጀትና ተቃዋሚውን ከምርጫ ውጪ ለማድረግና በሰበብ አስባቡ ለመወንጀል እንዲያመች የታሰበ ነው፡፡
ሁማን ራይትስ ዎች (2010)
ኢትዮጵያዊያን በነጻ መናገር፤ ሃሳባቸውን መግለጽ፤የፖለቲካ ስብሰባዎችን ለማዘጋጅት፤የመንግስትን መግለጫዎችና አግባብነት የሌላቸውን አዋጆች ለመቃወምም ሆነ የተለየ ሃሳብ ለማቅረብ፤ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ፤ በነጻ ፕሬስ ሃሳባቸውን ማስፈር ጨርሶ የማይችሉበት የፍርሃትና የጭንቀት ሁኔታ ውስጥ ናቸው፡፡የዴሞክራሲ ቴክኒካል አሰራር ፍሬም ለዘለቄታው ማታለያና የገዢው ፓርቲ የመከላከያ ብረት ግንብ ሆኖ የገዢውን ፓርቲ ፍላጎት ማሟያ ብቻ እንዲሆን የታቀደ ከመሆኑም አልፎ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣኖች ለሚያደርሱት ሕዝባዊ ግፍ ተጠያቂነት የለባቸውም፡፡
የዓለም የፋይናንስ እውነታ ዎል ስትሪት ጆርናል (2011)
ኢትዮጵያ ከ2000 እስከ 2009 ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያየ እኩይ ድርጊት ብክነት 11፣7 ቢሊዮን ዶላር ተመዝብራለች፡፡የኤኮኖሚው አቅም ደካማና የኑሮ ውድነት ሕዝቡን አላላውስ ብሎ ወጥሮ በያዘው ሃገር ላይ እንዲህ አይነት ብክነትና ስርቆት እጅጉን አሳዛኝ ነው፡፡ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድም አውቀው እንዳላወቁ በመሆን ባለስልጣናት ከባለስላጣናት ጋር በመወዳጀት በ2009 ብቻ ከሕግ ውጪ 3.26 ቢሊዮን ዶላር ካለፉት ሁለት ዓመታት በእጥፉ ከሃገር ወጥቷል፡፡
የጋዜጠኞች መብት ጠባቂ ኮሚቴ (2011)
በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በማሰር፤ በማሰቃየት፤ በማንገላታት ዝና ካተረፉት ሃገራት መሃል ከኤርትራ ቀጥላ የግፍ ከረጢት በመባል የተመዘገበችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ግፉና መከራው እያሰቃያቸው ብዙ የነጻው ፕሬስ አባላት ሃገራቸውን ጥለው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ይህም በቁጥር በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ መለስ ግን፤ለኖርዌጂያኑ (Aftenposten) ጋዜጣ‹‹ ለሕግ ልዕልና መከበር ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ ሰብአዊ ምብትንም በአግባቡ እናከብራለን፡፡ሃገራችን የህዝቦቿ የዴሞክራሲ መብት በአግባቡ የተከበረባት ሃገር ነች››በማለት የሌለ ነገር አለ በማለት ይቀላምዳል፡፡
ሁማን ራይትስ ዎች (2011)
የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ሽብርተኛነት መከላከል ያወጣውን የይስሙላ አዋጁን ሰላማዊ ሰዎችን ለማሰርና ለማሰቃየት ሊጠቀምበት የፈጠረው ነው፡፡የጸረ ሽብር ሕጉ በራሱ ትልቁ ችግር ነው፡፡ዓለም አቀፉ ሕብርተሰብ በተለይም የአውሮፓ ዩኒየን፤ ዩናይትድ ስቴትስ፤ዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት ይህን ሕግ ለምን ሰላማዊ እንቅስቃሴንና የሰላመዊውን ሕዝብ ድምጽ ለማፈኛነት እንደዘረጋው ሊጠይቁት ተገቢ ነው፡፡
የኮንግሬስማን ዶናልድ ፔይን ዘገባ (2007)
ሰብአዊ መብት 2003 ( ዴሞክራሲና ተጠያቂነት አክት 2007 የተወካዮች ምክር ቤትን ድጋፍ አግኝቶ በኦክቶበር 2 2007 አለፈ) የአገር አስተዳደር ሚኒስቴር የሰብአዊ መብትን በመደገፍ አንድ ማዕከል ፈጥሮ ለሃገር በቀል የሰብአዊ መበት ተሟጋቾች የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግበትን ዘዴ መቀየስ አለበት፡፡ሕጉ፤የዴሞክራሲን ሂደት በመደገፍ የዴሞክራሲን እውነታ ማጎልበትን ሲደግፍ፤የአሜሪካ መንግስት ሰብአዊ መብትን ለማደርጀት የሚያደርገውን ጥረትና እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የሚያውክ ከሆነ ይህን መሳዩን የሰብአዊ መብት አፈና ለማቆም የሚደረገው እርዳታ ሁሉ ከሰብአዊ መበት መከበር ጋር ተጓዳኝ መሆን እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡የ2005 ውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ፤ ከመንግስት በኩል ያስከተለውን ኢሰብአዊና ጸረ ዴሞክራሲ ተግባር አስመልክቶ የደህንነት ክፍሉን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡
የአሜሪካው ሴኔተር ረስ ፌይንጎልድ እና ፓትሪክ ሌሂ ረቂቀ ህግ 3457 (2008) ላይ አስተያየታቸው
ሚስተር ፌይን ጎልድ፤ – ሚስተር ፕሬዜዳንት፤በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትንና የዴሞክራሲን ረቂቀ ህግ 3457ን ድጋፍ ለማስታወቅ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፡፡የዚህ ረቂቀ ህግ ዋናው ጥቅም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖሊሲውን ግብ ለማረጋገጥና እውነተኛው ዴሞክራሲ ከተጫነበት ጫና ተላቆ ለሕዝቡ ጠቀሜታ የሚውልበትን ነጻ ሂደት ለማረጋገጥ ነው፡፡ ነጻ የሆነ የህግ ስርአትና የሕግ የበላይነት፤የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች መከበርን፤በነጻው ሚዲያ ላይ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የተጣለውን አፋኝ ገደብ ማስንሳት፡፡… እየባሰባት በሚሄደው የፖለቲካ ውጥረት ላይ ሰምተን አልሰማንም አይተን አላየንም በማለት ችላ ካልነው፤በግፍ ወደ ወህኒ የሚጣሉትን ንጹሃን ከረሳናቸው፤መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ገደብ ከተጣለባቸውና ስራቸው እንዲዳከም ሲደረግ ችላ ካልን፤በኦጋዴን አስተዳደር ቀደም ሲል በኦሮሚያ፤በአማራው፤በጋምቤላ የተፈጸመውን በቸልታ እንዳለፍነው ሁሉ አሁንም ሰዎች በግፍ ሲገደሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ካልን፤ከተጠያቂነት አናመልጥም………
2010 የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የሜይ 2010 የምርጫ ዘገባ
በአብዛኛው የሃገሪቱ ክልሎች የገዢው ፓርቲና መንግስታዊ እንቅስቃሴዎችና ምርጫው ላይ የነበረው ልዩነት ጨርሶ አይታይም ነበር፡፡ ገዢው ፓርቲ መልሶ መንግስት ነው፡፡የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢ ቡድን፤የመንግስትን መገልገያና ሌሎችም ያና መጠቀሚያ ሲውሉ ተመልክቶ ታዝቧል፡፡ገዢው ፓርቲና አጋር ፓርቲዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ547 መቀመጫዎች 544ቱን አሸነፉ፡፡ በዚህም የምርጫው ሂደት ዓለም አቀፍ ደረጃውን መመዘኛ ማሟላት አቅቶታል፡፡ግልጽነት አልነበረውም እንዲሁም ለሁሉም ምርጫ ተፎካካሪዎች መድሎ የሌለበት ሂደትም አላሳየም፡፡ ለገዢው ፓርቲ በሁሉም መልኩ የወገነ ሁኔታ ነበረው፡፡
የመለስ መልስ፡- ለ2010 ለአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢ ኮሚቴ ሪፖርት
የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ዘገባ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ያለበት ቆሻሻ ነው፡፡ዘገባው ስለእኛ ምርጫ አይደለም፡፡ገዢው ፓርቲ በመፈርጠሙ የተነሳ የአንዳንድ አውሮፓውያን ኒዮ-ሊበራልስ የቅናትና ምቀኝነት ዘገባ ነው፡፡ማንም ወረቀትና ብዕር ያለው የፈለገውን መሞንጨር ይችላል፡፡
ይህ ነው የመለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ያለው ዴሞክራዚ!
ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ:: http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic


Hello Professor Alemayehu G/ Mariam,
I am one of the admirers of your intellectual writings with indepth research and thoughtfulness. This is my first comment on your articles. According to your presentation, President Obama’s view and that of Prime MInister Meles are contrary on issues relating to democracy and economic growth. H.E. Prime Minister Meles tried to explain the benefits of democracy to a multi-ethnic country like Ethiopia and also he stated that there is no direct relationship between economic growth and democracy. Though I am not an economist, I agree with the assessment of H.E. Prime Minister Meles on this issue for the following reason. For example, China is not a democratic country and yet it has shown an extra ordinary economic growth and became the second biggest economy which has vertaken the so-called the democratic model countries such as Japan, UK, France, and Germany and anticipated to do the same to USA.
Ethiopia may not be a perfect democracy in your view or in President Obama’s standard, but it has demonstrated a consecutive economic growth for the last seven years and this has been confirmed by IMF and World bank, which are independent institutions. So Mr. Mele’s analysis was based on practical aspects that are revealed around the world. In fact, we are seeing turmoil and economic crisis in the western countries who advocated democracy. So where is a direct relationship between democracy and economic growth? I think we have to see the merits and demerits of democracy and to what degree it contibutes to economic growth based on the facts on ground.
I have no objections to further demands on our government to improve democratic institutions as indicated by President Obama. Our country is at the embryonic stage of democracy and we have to participate as citizens in betterment of its system of governance, fighting against corruption, promoting independent judiciary and press, strong developmental private sector, strong parliament, faithfiul police, and civic organizations. We have all these things in place and the government is calling upon all Ethiopians in Diaspora to participate in the development of our country.
Besides, our constitution guarantees all democratic rights to its citizens. Some individuals and organizations are getting into trouble only when they breach the spirit and the letter of the constitution. For example, if someone tries to carry out a free press in association with terrorist organizations which are sworn enemies of Ethiopia who took up arms against the government and people of Ethiopia, the government has no choice but bringing them to face the might of the law. The government does not interefere in the interpretation and decision of the courts. USA would do the same if someone associates with Al Qaeda and posts online the comments that promote their views. You know very well that Shabia is working with Al Shebaba, ONLF, G7, etc. So if anyone propagates and supports their views and attempts to incite violence in the country, government is duty bound to solve this problem by nipping at its bud. You will do the same if you were vested with this power of governiing the country.
None of the opposition parties who are vociferous to fight against our government are more democratic than the current regime. They are not tested yet and we have fear of the unknown concerning them. They don’t have coherent policies and they are not committed to them. They simply put them on the paper as their manifesto and yet we see them bickering and fighting one another. There is no democracy even within themselves. How can these parties manage to govern a great country like Ethiopia with diverse ethnic and cultural background while they are not even able to lead their own house in order. They have no grass-roots establishments. They only attempt to entice the elite with rosy and false hopes and most of the times with lies against the record of the current regime.
Let me tell you some of the lies that I noticed: they don’t recognize that there is developmental growth in Ethiopia, they deny that there is freedom of region and try to incite Muslims and Christians alike, they say that the government is sabotaging against refugees to be deported from other countries, they exaggerate land allocation for investors as land-grab, they deny the fact that the government is doing voluntary villagization, they misinform the public about peace-keeping role of our armed forces as well as defending territorial integrity of our country, they sympathize and work together with any group or country that de-estabilize our country. How do you think Ethiopians can replace the current regime with these traitors, power-mongers and liers?
There is a saying, “better the devil you know than the devil you don’t”. Ethiopians know the current regime very well with all its pros and cons even though we don’t agree with everything it does. It has implemented democratic rights to all its citizens, nations, nationities and peoples of all regions. Each region is administered by its own people. You know very well that in all previous regimes, the whole Ethiopia was ruled by Amharas up to Woreda level regardless of availability of educated people in that region. We were subjects to them against our will and we were made to be inferior and treated like second class citizens (Chisegna). Our labor was exploited and all our produces were snatched away by the land-lords. We were citizens without land. Now everyone equal in fron to of the law and the land belong to the people and government of Ethiopia. It is given to every citizen for free under lease-hold policy.
The opposition groups are now talking about Ethiopianization in order to dengrade the rights ushered to these oppressed classes, ethnic groups, nations, nationalities and peoples of Ethiopia and to resuscitate the views of the old Amhara regime. We know very well that all of us are Ethiopians and yet we want to be respected without discrimination due to our ethnic, racial, religious, cultural, and linguistic differences. We appreciate the current regime for implementing these democratic rights for all citizens of Ethiopia. We are made to appreciate our diversity in unity and vice versa. So we don’t trust the motives, objectives and goals of the opposition groups that fight against our people and government. They cannot create Arab Spring in Ethiopia as they envision because they are not fighting for the rights of Ethiopian people. Ethiopians know very well their enemies and allies. So please educate us with the right concept and use your influence to unite us to build Ethiopia in stead of cooperating with those who are hell bent to demolish our country and all its development endeavors. Let us keep in touch.
Sinceely,
Alemu